=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
አሏህ ባሮቹን ያመልኩት ዘንድ ፈጠራቸው ፤ ያመሰግኑትም ዘንድ መገባቸው። ሆኖም ግን ብዙዎቹ እሱን ትተው ሌሎችን ተገዙ ፣ ሌላውን አመሰገኑ። ምክኒያቱም የክህደት፤ ጥሩውን በመጥፎ የመመለስ እና ፀጋዎችን የመካድ ተፈጥሮ በነፍሶቻቸው ውስጥ ሰፊውን ቦታ ይይዛልና። በመሆኑም እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች የዋልክላቸውን ውለታ ቢክዱ አትደንግጥ ፤ የሠራህላቸውን መልካም ነገር ቢዘነጉ ፤ ያደረከውን በጐ ነገር ቢረሱ ፤ ምናልባትም በጠላትነት ቢፈርጁህ ፤ በተቀበረ የምቀኝነት መድፍ ቢተኩሱህ አትደነቅ። ይህን ሁሉ የሚያደርጉትም በሠራኸው ጥፋት ሳይሆን በጐውን ስለዋልክላቸው ብቻ ነው።
-«<({አል-ቁርአን 9:74})>»-
«አሏህም ከችሮታው ነብዩም እንደዚሁ ያከበራቸው መሆኑን እንጂ ሌላን አልጠሉም»
የገሃዱን ዓለም መዝገብ አገላብጠህ ተመልከት ፤ ምእራፎቹ በሙሉ የዚያን አባት ታሪክ ያተቱ ናቸው። ልጁን አሳድጐ ፣ አብልቶ ፣ አጠጥቶ ፣ አልብሶ ፣ በመልካም ስነ-ምግባር አንፆ ፣ አስተምሮ ፣ ልጁ እንዲተኛለት እሱ ዕንቅልፍ አጥቶ ፣ እንዲጠግብለት እሱ ተርቦ ፣ እንዲያርፍለት ደክሞ ፤ ይሄ ልጅ አድጐ ጉልበቱ በጠነከረ ጊዜ አባቱን በማገልገልና በማስደሰት ፈንታ የእብድ ውሻ ያክል ሆነበት ፣ አዋረደው ፣ አሰቃየው ፣ አስቸገረው ፣ መከራ አሳየው ፣ ጮኸበት ጠንቅ ሆነበት።
አዋጅ....... ፍጥረተ ጠማማዎቹና የሞራል ከስካሾቹ የውለታዎቻቸውን መዝገብ ያቃጠሉባቸው ሰዎች ይረጋጉ..... አይጨነቁ። ካዝናዎቹ መቼም ባዶ በማይሆኑበት ___ታ ዘንድ በሚያገኙት ምንዳም ይደሰቱ...... ይፅናኑ።
ይህ ንግግር ለሰው በጐ መዋልን እንድትተው አይጋብዝህም ፤ ለሌላው መልካም መስራትን አይከለክልህም። ባይሆን ለሰው የዋልካቸው ውለታዎችና የሰራሃቸው መልካም ስራዎች በመጥፎ ሊመለሱ እንደሚችሉ ገምተህ እንድትጠነክር ይረዳሃል። ይሰሩት በነበረውም ተንኮል አትበሳጭ።
መልካም ነገርን ለአሏህ ብለህ ስራው ምክኒያቱም ሰው ቢያወድስህም ቢያወግዝህም አሸናፊው አንተነህና። የከሃዲ ክህደትም ሆነ የማንም ሰው ንቀት አይጐዳህም። መልካም ሰሪው አንተ በመሆንህ እና ክፋት ሰሪው እርሱ በመሆኑ አሏህን አመስግነው። ለጋሽ እጅ ከተቀባይ ትሻላለችና።
-«<({አል-ቁርአን 76:9})>»-
«የምናበላችሁ ለአሏህ ውዴታ ብቻ ነው፤ ከናንተ ዋጋንም ማመስገንም አንፈልግም»
ብዙ ብልህ ሰዎች በሁካታ ጊዜ ከክህደት ባልደረቦች ተግባራት ተበሳጭተዋል። የላቀውም ራዕይ (ቁርአን) የነዚህን ክፍሎች አመፅና እብሪት ሲገልፅ እንዲህ ማለቱን እንዳልሰሙ.....
-«<({አል-ቁርአን 10:12})>»-
«ወደ አገኘው ጉዳት እንዳልጠራን ሆኖ ያልፋል»
ለሰነፍ ብእር ሰጥተኸው የዘለፋ ቃለትን ቢፅፍልህ አትገረም። ለውለታቢስ እንዲመረኮዝባት ወይም ለበጐቹ ቅጠል እንዲያራግፍበት ዱላ ሰጥተኸው እራስህን መልሶ ቢመታህም አትደነቅ። ምክኒያቱም የዚህ ዓይነቶቹ በክህደት ከፈን የተገነዙ ሰዎች ከፈጣሪያቸው ጋር ያላቸው ባህሪ እንዲህ ነው። ታዲያ ከኔና ካንተ ጋር እንዴት ይሁኑ?!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|